አሸዋ ቴክኖሎጂ ሶሉሽን አ.ማ የሶፍትዌር ንግድ ስራ ጀመረ፡፡

አሸዋ ቴክኖሎጂ ልዩ ነው፡፡
ልዩነት በሚፈጥር ትልቅ ችግር በሚፈታ የህዝባችንን ህይወት ቀላል፣ የተሻለ እና የዘመነ ማድረግ የሚያስችለዉን ድንቅ ዘርፍ መቀላቀሉ ይበል የሚያሰኝ ነው። “በዘርፉ ትልቅ ልምድ ያካበተው አሸዋ ቴክኖሎጂ ሶፍትዌር መስራት ደስታችን ነው እና የምንሸጥላቸውም እሱ ነው” ይላል we deliver satisfactions!! It is our passion!! የኛው የሆነው አሸዋ ቴክኖሎጂ በድንቅ ድንቅ ቴክኖሎጂዎች ለየት ባለ መልኩ ለግል ድርጅቶች እና ለመንግስት ተቋማቶች፣ ለስራ ፈጣሪዎች፣ የተለያዩ የሶፍትዌር ቴክኖሎጂዎችን በዋና መስሪያ ቤቱ አስተዋዉቋል!!!

ሁሉንም ድርጅቶች በቴክኖሎጂ የሚያግዝ፣ የሚያዘምን እና የተሻሉ እንዲሆኑ የሚረዳው አሸዋ ቴክኖሎጂ ዘመኑን የሚመጥኑ ለትግበራ ዝግጁ የሆኑ እና በፍላጎት መሰረት የሚሰሩ የዌብሳይት ወይም በይነ መረብ እና የሞባይል አፕልኬሽኖችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለመስራት እና ለመሸጥ ሙሉ ዝግጅቱን ጨርሶ ነው ወደ ስራ የገባው። ቴክኖሎጂዎቹ በዋናነት የትንንሽ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን ችግር የሚቀርፉ፣ ይወጣ የነበረዉን የዉጭ ምንዛሬ በአገር ዉስጥ ምርት በመተካት እና ለሰብሰሃራን አፍሪካ ገበያም የሚቀርብ በመሆኑ የውጭ ምንዛሬ የሚያስገኝ መሆኑን አቶ ዳንኤል በቀለ ተናግረዋል።

ለራሱ በመስራት የጀመረው የብዙዎችን ትኩረት የሳበው አሸዋ ቴክኖሎጂ ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች እና ምርቶች ዉስጥ ኢአርፒ ሶፍትዌር ቴክኖሎጂ እንደ ት/ት ቤቶች፣ ሆስፒታሎች፣ሆቴሎች፣ አምራቾች፣ ባለህንጻዎች፣ ፋርማሲዎች፣ ነጋዴዎች ለሁሉም ድርጅቶች በመስፈርታቸው መሰረት እንሰራለን በተጨማሪም ሶፍትዌር እንደ ሰርቪስ እናም በአግሪ ቴክ የግብርና ማሳ መቆጣጠሪያ እና መሸጫ ሱቅ ሶፍትዌር እንደ ሰርቪስ የድርጅት ዌብሳይት ማንኛውንም የቢዝነስ ሃሳብ ወደ ሶስፍትዌር ቴክኖሎጂ በመስፈርታቸው መሰረት እንቀይራለን ብሏል!!

ይህ ቴክኖሎጂ ተቋምዎትን የሚያዘምን እና ከወረቀት ንክኪ ዉጭ ድጅታል የሚያደርግ ነው። ይህን ለማሳለጥ እና አስተማማኝ ስራን ለህዝቡ ለማቅረብ ተቋሙ በራሱ ካሉት ኢንጅነሮች ጥርቅም በተጨማሪም ከእነ አይቢኤም, AFRICOM እና FOR ጋር በአጋርነት ለመስራት ስምምነት ማድረጉ የሚታወስ ነው።

አሸዋ በኢኮመርስ እና ሎጂስቲክስ ላይ ስራውን ጀምሮ ባጭር ጊዜ በዘርፉ ፈር ቀዳጅ በተደራጄ መልኩ በአይነቱ ልዩ በሆነው ዘርፍ በሺ የሚቆጠሩ ደንበኞችን እያገለገለ እንደሆነ ይታወቃል፡፡