የአዲስ አበባ ነጋዴዎች ማህበርና አሸዋ ቴክኖሎጂ ሶሉሽንስ አክስዮን ማህበር ጥር 09 ቀን 2015 በሳፋየር አዲስ ሆቴል በጋራ ለመስራት ተስማሙ።

የአዲስ አበባ ነጋዴዎች ማህበር እና አሸዋ ቴክኖሎጂ ሶሉሽን አክስዮን ማህበር በጋራ በመስራት የዘልማዱን የንግድ ስርአት በዲጅታል ቴክኖሎጂ ለማዘመን የስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡ የፊርማ ሥነ ስርዓቱም በአዲስ አበባ ነጋዴዎች ማህበር ፕሬዝዳንት ዘሀራ መሐመድ እና በአሸዋ ቴክኖሎጂ ሶሉሽንስ አ.ማ መስራችና ዋና ሥራ አስኪያጅ ዳንኤል በቀለ መካከል የተደረገ ሲሆን፤ በመድረኩም የማህበራቱ ተወካዮች፣ የመንግስት የሥራ ሀላፊዎች እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተውበታል።

ሁለቱ የንግድ ተቋማት በጋራ ለመስራት ዋነኛ አላማቸው፤ በነጋዴዎች እና በህብረተሰቡ መካከል ያለውን አላስፈላጊ የንግድ ሰንሰለት ለመበጠስ፣ ለመንግስት ቁጥጥር አመቺ አለመሆንን ለማስወገድ፣ ነጋዴው በልፋቱ ልክ እንዲጠቀም ማድረግን፣ጠንካራ የትርፋ እና የገበያ ትሥስር እንዲኖር ማድረግን እንዲሁም ተጠያቂነት እና ተወዳዳሪ የገበያ እድል እንዲፈጠር ለማድረግ እና የማህበረሰባችንን ጊዜ ገንዘብ እና ጉልበት መቆጠብ ህይወትን ማዘመን ለማስቻል ያለመ ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ነጋዴዎች ማህበር ፕሬዘዳንት ወ/ሮ ዘሀራ መሀመድ ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም እየታየ ያለውን የዋጋ ግሽበት መቀነስ፤ ህጋዊ ነጋዴዎቹን ማሰልጠን እና ትርፋማ ማድረግ፤ የደንበኞችን ድካም መቀነስ፤ የነጋዴዎችን ጊዜ መቆጠብ፤ ኦርጅናል እቃዎችን ማቅረብ፤ ነጋዴዎችን በቴክኖሎጂ በመደገፍ ተጠቃሚነታቸውን በማሳደግ ህገወጥ ደላሎችን የማውጣት አላማ እንደለው የአሸዋ ቴክኖሎጂ ሶሉሽን አክስዮን ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ ዳንኤል በቀለ አስረድተዋል፡፡

ባሁኑ ሰአት በሺህ የሚቆጠሩ ነጋዴዎች ምርት እና አገልግለሎታቸውን በአሸዋ ዶትኮም በኩል የሚያስተዋውቁበት ቨርችዋል የሆነ ሱቅ እየከፈቱ እና እየሸጡ ያሉ ሲሆን በአዲስ አበባ ነጋዴዎች ማህበር ስርም ላሉ ምርታቸውን በቀጥታ ለደንበኞቹ የሚያደርሱበት እድል ማህበሩ ማመቻቼቱንም ገልጿል፡፡ በግብይቱም አልባሳት፤ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፤ የግብርና ውጤቶች ፤ የጤና፤ የውበት መጠበቂያ ምርቶች እንዲሁም ሌሎችን ደንበኞች ያገኛሉ ተብሏል፡፡

በአህጉራችን አፍሪካ ብሎም በሀገራችን ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂው ከፍተኛ መነቃቃት እየመጣ ሲሆን መንግስትም እስከ 2025 ዲጅታል ኢትዮጵያን በመገንባት ሂደት ላይ መሆኑ የሚታወስ ነው::

 

Leave a Comment

Required fields are marked *