አሸዋ ቴክኖሎጂ ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በጋራ ለመስራት ተፈራረመ!

አሸዋ ቴክኖሎጂ ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በጋራ ለመስራት ተፈራረመ።


አሸዋ ቴክኖሎጂ ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርሲቲ ጋር አብሮ መስራት በሚያስችላቸዉ ጉዳይ ላይ ለአምስት አመት የሚቆይ የሰነድ የፊርማ ስነ- ስርዓት አካሂዷል።የፊርማ ስነ-ስርአቱ ላይ የሁለቱም ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተከናዉኗል።


የአሸዋ ቴክኖሎጂ ሶሉሽን አክሲዮን ማህበር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዳንኤል በቀለ "ከዩኒቨርስቲው ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችለንን የሰነድ ፊርማ ማከናወናችን ለሀገር ችግር ፈቺ የሆኑ ትልልቅ ፕሮጀክቶችን ለመስራት በር ከፋች ነዉ" ብለዋል።


"ተማሪዎች ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ የሆኑ የቴክኖሎጂ ዉጤቶችን እንዲሰሩ እንደ አሸዋ ቴክኖሎጂ ያሉ ተቋማት ጋር በጋራ መስራታችን ኢንዱስትሪዉ እንዲነቃቃ ያደርገዋል" ሲሉ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ የአካዳሚክስ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ከማል ኢብራሒም(ዶክተር) አብራርተዋል።


የመግባቢያ ሰነዱ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚሰራ ተጠቁሟል።


👉አሸዋ ቴክኖሎጂ በዩኒቨርሲቲው በኩል ለሚመጡ ኢንደስትሪዎች አንደየፍላጎታቸው ብራንዳቸውን የሚያሳድጉበትና በራሳቸው የገበያ ትስስር የሚፈጥሩበትን የዲጂታል ማርኬቲግ እና የኢኮሜርስ ስልጠናዎችን እንዲሁም ዌብሳይት ግንባታዎችን ያመቻቻል፡፡

👉አሸዋ ቴክኖሎጂ ዓለም አቀፍ ስታንዳርድ ያላቸውን የቴክኖሎጂ አገልግሎቶቹን እንደ ኢአርፒ ፣ ከስተም ሶፍትዌር ፣ ነሃቢ እና የክላውድ አገልግሎት እንዲሁም ማንኛውንም የቴክኖሎጂ ፈጠራዎችን ይሰጣል ፡፡  


👉የዲጂታል ማርኬቲንግ እና የኢኮሜርስ ስልጠናዎችን በመስጠት ኢንዱስትሪዎች በጎ ገፅታቸውን እንዲገነቡ እና ምርታማነታቸውን እንዲያሳድጉ ያግዛል። 

👉ለህብረተሰቡ ችግር ፈቺ የሆኑ ስራዎች ላይ ትኩረት እንዲያደርጉና አስፈላጊ የሆኑ የቴክኖሎጂ ግብአቶችን ለምርቶቻቸው ወይም ለአገልግሎቶቻቸው መጠቀም እንዲችሉ እና በልፋታቸው ልክ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ሙያዊ ድጋፍ ይሰጣል። 

👉ስምምነቱን ለሚደግፉ ሌሎች ፍላጎት ያላቸው ድርጅቶች (መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ የመንግስት መስሪያ ቤቶች፣ የግል ኩባንያዎች፣ ማህበራት እና ሌሎች) እንዲሳተፉ ምቹ ሁኔታዎችን እንደሚያመቻች ተገልጿል።

አሸዋ ቴክ ህዳር 16/2017

 

Leave a Comment

Required fields are marked *

Your name:
Email:
Website | Blog:
Your tought:

Let's Turn Your Vision into Reality: Contact Ashewa Today!

Ready to unleash the power of technology for your business? We're here to help you transform your ideas into game-changing solutions.


Schedule a Free Consultation

Discuss your project needs and get expert advice from our team.


Request a Quote

Get a tailored proposal based on your specific requirements.


Explore our Case Studies

See how we've helped businesses like yours achieve success.

Reach us through (Phone, Email, Telegram or WhatsApp Chat).


Join our Community

Stay informed about the latest tech trends and industry insights


Don't wait

Contact us today and let's start building something amazing together!

Ashewa Technology Solutions SC
We typically replies within an hour

Kasse Assefa
Hi there 👋

How can we help you?
×
Chat with Us