በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነው የራስን ድረገጽ በራስ መገንቢያ ቴክኖሎጂ ይፋ ሆነ

አሸዋ ቴክኖሎጂ ሶሉሽን አክስዮን ማህበር በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የሆነውን ድረ-ገጽ መገንቢያ እና ERP SAAS ስሪ ማስጀመሪያ ቴክኖሎጂን በዛሬው ዕለት ይፋ አደረጉአል ።

በሀገራችን ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂው ከፍተኛ መነቃቃት እየመጣ ሲሆን መንግስትም እሰከ 2025 ዲጅታል ኢትዮጵያን በመገንባት ሂደት ላይ መሆኑ የሚታወቅ ነው።በዚሁ መሠረት አሸዋ ቴክኖሎጂ የዲጂታል ዘርፉን ለማዘመን በስማርት ሶሊዩሽን እንደ SaaS (software as a service )፣ ኢ ኮሜርስ (Ashewa.com)፣ በ ኢ - ለርኒንግ፣ እና ሎጂስቲክና ዌርሀውስ ሰርቪስ አገልግሎቶችን እየሰራም ይገኛል፡፡

አሁን ደግሞ በሃገራችን የመጀመሪያ የሆነውን የድረገጽ መተግበሪያ እና enterprise resource planning (erp)saas ስራ ከአሸዋ ቴክኖሎጂ መቅረቡን የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ዳንኤል በቀለ ገልፀዋል።

ከነዚህ ቴክኖሎጂዎች መካከል ስማርት ሳይት ቢውልደር ( Smart site builder ) አንደኛው ሲሆን ይህም አንድ ሰው በራሱ የራሱን ዌብሳይት ወይም ድረ ገጽ መገንባት እንዲችል የሚያደርግ እንዲሁም ኢ አር ፒ (ERP SAAS ) የሚባለው ደግሞ አጠቃላይ ተቋማትን በስልካችን ወይም በላፕቶፓችን መቆጣጠር እንድንችል የሚያደርግ ፕላት ፎርም መሆኑን ከነ ተጨማሪ ማብራሪያ የአሸዋ የቴክኖሎጂ ኢንጅነሪንግ ዲፓርትመንት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አመንሲሳ ደረጀ አቅርበዋል።

እነዚህ ቴክኖሎጂዎች በአለም ገበያ ላይ በበርካታ ሚሊዮኖች የሚገዙ ቢሆንም በአሸዋ ቴክኖሎጂ በኩል በተመጣጣኝ ክፍያ መጠቀም የሚቻል እንደሆነ ስራ አስኪያጁ የተናገሩ ሲሆን ሶፍትዌሮችን በተጠቃሚ ፍላጎት ማበልፀግ የሚያስችል አዲስ አሰራር መዘርጋቱም በተነገረበት መድረክ ከተለያዮ የሚዲያ ተቁአማት የተጋበዙ ባለሙያዎችም ለ ተጨማሪ ማብራሪያ ጥያቄዎችን አንስተዋል።

አሸዋ ቴክኖሎጂ ሶሉሽን አክስዮን ማህበር የሁላችን ጠላት የሆነውን ድህነትን ለመዋጋት እና ለመጣል ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ ባለው የቴክኖሎጂ ዘርፍ ላይ እየሰራ ያለ ተቋማት ሲሆን፤ በአስራ አንድ የቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ ለመስራት ተመዝግቦ በአገር ውስጥና በውጭ አገር በሠሩና በተማሩ ሰዎች የተቋቋመ በስራ ላይ የሚገኝ አገር በቀል የቴክኖሎጂ ድርጅት ነው።

 

1 Comments

yayeesew birhan

(ERP SAAS) በጣም ደስ የሚል ነው። በሃገራችን በመሆኑ ተመራጭ ያደርገዋል።

Leave a Comment

Required fields are marked *

Your name:
Email:
Website | Blog:
Your tought:

Let's Turn Your Vision into Reality: Contact Ashewa Today!

Ready to unleash the power of technology for your business? We're here to help you transform your ideas into game-changing solutions.


Schedule a Free Consultation

Discuss your project needs and get expert advice from our team.


Request a Quote

Get a tailored proposal based on your specific requirements.


Explore our Case Studies

See how we've helped businesses like yours achieve success.

Reach us through (Phone, Email, Telegram or WhatsApp Chat).


Join our Community

Stay informed about the latest tech trends and industry insights


Don't wait

Contact us today and let's start building something amazing together!

Ashewa Technology Solutions SC
We typically replies within an hour

Kasse Assefa
Hi there 👋

How can we help you?
×
Chat with Us